Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኦሮሚያ ክልል 2 ነጥብ 5 ሚሊየን የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መጽሐፍት ለስርጭት ተዘጋጅተዋል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ በአዲሱ ስርአተ ትምህርት የታተሙ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ተጨማሪ መጽሐፍት ለስርጭት መዘጋጀታቸውን የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ይህም በአዲሱ የትምህርት ዘመን ተዘጋጅተው በክልሉ የተሰራጩ መጽሐፍትን ቁጥር 11 ሚሊየን እንደሚያደርሰው የቢሮው ምክትል ሃላፊ ኤፍሬም ተሰማ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ከሚፈለገው የመጽሐፍት ቁጥር አንፃር በቂ አይደለም ያሉት ምክትል ሃላፊው÷ ችግሩን ለመፍታት በመጪዎቹ ሶስት አመታት የሚተገበር እቅድ ተዘጋጅቷል ነው ያሉት፡፡

በአፈወርቅ እያዩ

Exit mobile version