አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 29፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኬንያ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋና የመሬት መንሸራተት የ200 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል። በአደጋው ህይወታቸው ካለፈው 200 ሰዎች በተጨማሪ 100 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው ነው የተነገረው። ከዚያም ባለፈ በሺዎች የሚቆጠሩ ሔክታር ሰብሎች መውደማቸውን የሀገሪቱ መንግስት ባወጣው መግለጫ ገልጿል። ባለፈው ወር መዝነብ የጀመረው ከባድ ዝናብ ለሳምንታት ይቀጥላል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን÷ ሁለት የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድቦች ባንኮቻቸው ሊፈነዱ ይችላሉ የሚል ስጋት መኖሩም ነው የተነገረው። በዚህም ከግድቡ በታች የሚኖሩ ዜጎች አካባቢውን ለቀው ከፍታማ ቦታ ላይ እንዲሰፍሩ ተነግሯቸዋል ነው የተባለው። ከዚያም ባሻገር የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋው በሀገሪቱ የ26 ሰዎችን ሕይወት ያጠፋውን የኮርናቫይረስ ስርጭትን ለማስቀረት ችግር እንደሚፈጥር የኬንያ መንግስት አስታውቋል ።
ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision