የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኳታር አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Amele Demsew

August 08, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከኳታር ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ሐማድ ቢን ሞሐመድ አል-ዶሳሪ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም÷ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

በተጨማሪም÷ ሀገራቱ በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በጤና ነክ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።