የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ኮሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

By Amele Demsew

August 08, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓርክ ጂን ለሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ሚኒስትሩ ሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡