Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሩሲያና ኢራን በንግድ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ እና ኢራን በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የማሳደግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

የሩሲያ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዲሚትሪ ቮላቫች ከኢራን አመራሮች ጋር በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማሳደግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ሀገራቱ በነጻ የንግድ ቀጠናዎቻቸው ላይ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተዋል፡፡

የሞስኮ እና ቴሕራን የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነት የማጠናከር ፍላጎት በምዕራባያን የተጣለባቸውን ማዕቀብ ለመቀልበስ ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

በሩሲያና ካስፒያን ክልል ሀገራት እና ወደ ሰሜን-ደቡብ ዓለም አቀፍ የትራንስፖርት ኮሪደር ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ እንደሚያስችልም ተጠቁሟል፡፡

የሀገራቱ የኢኮኖሚ፣ የትራንስፖርት እና የሎጂስቲክስ ትብብርን መጠናከር ከምዕራባውያን የሚመጣባቻን ጫና ለመገዳደር ሚናው የጎላ መሆኑን አርቲ ዘግቧል፡፡

በተያዘው የፈረንጆች ዓመት መጀመሪያ ኢራን እና ሩሲያ የሸቀጦች፣ የአገልግሎቶች እና የሰራተኞች እንቅስቃሴ በነፃነት እንዲዘዋወር የሚያስችል ነጻ የንግድ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

Exit mobile version