Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በፖሊስ አባላት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ከነ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የጨፌ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አባላት በወረዳ 11 በተለምዶ ፀበል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለፀጥታ ስራ ሲባል ትናንት ሃምሌ 27 ቀን 2015 ዓ/ም ምሽት ድንገተኛ ፍተሻ ሲካሄድ ነው ሊያዝ የቻለው፡፡

ግለሰቡ በታክሲ ተሳፍሮ እየተጓዘ እያለ የተጠቀሰው ቦታ ላይ ሲደርስ ፍተሻ መኖሩን በማወቁ ከታክሲው ወርዶ በእግሩ በመጓዝ ለማምለጥ ቢሞክርም የፖሊስ አባላት ተከታትለው አስቁመው በእጁ የያዘውን ፌስታል ሲፈትሹ 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር አግኝተው ከነተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር አውለውታል፡፡

በተጠርጣሪው ላይ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version