በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በሚደረገው ጥረት፣ በኢትዮጵያና አውሮፓ ህብረት ትብብር እንዲሁም ሁለቱን ወገኖች በሚጠቅሙ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
በኢትዮጵያ ሰላምን ለማጽናት መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረትና የሽግግር ፍትህን በተመለከተ መንግስት እያከናወነ ያለውን ተግባር አቶ ደመቀ አብራርተዋል፡፡
እንዲሁም በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን መሰረተ ልማቶች መልሶ መጠገንና የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል።
መንግስት የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ሙሉ ለሙሉ ለመተግበር የሚያደርገውን ጥረት በቁርጠኝነት እየፈጸመ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
መንግስት እያደረገ ያለውን ይህንን ጥረት እንደ አውሮፓ ህብረት ያሉ አጋሮች እንዲደግፉም አስምረውበታል።
የሱዳንን ሁኔታ በተመለከተም ችግሩ በዘላቂነት ሊፈታ የሚችለው በንግግርና በውይይት እንደሆነ ኢትዮጵያ እንደ ጎረቤት ሀገር እንደምታምንበት ገልጸው÷ የሰላም ማረጋገጥ ጥረቱ በሱዳናውያኑ ባለቤትነት መመራት እንደሚገባው ገልጸዋል።
ሰላም የማረጋገጥ ጥረቱ በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) እና በአፍሪካ ህብረት በኩል መካሄድ እንደሚገባውም ጨምረው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሱዳን ጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ 70 ሺህ ያህል ሰዎችን መቀበሏን ገልጸው÷ መንግስት እያደረገ ያለውን የሰብዓዊ ድጋፍ ሌሎች አካላት እንዲደግፉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
#Ethiopia
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television