የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል በ2016 በጀት ዓመት ከ265 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዷል

By Amele Demsew

August 04, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት ከ265 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ማቀዱን አስታውቋል፡፡

የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ በሰጡት መግለጫ÷ በ2016 በጀት ዓመት የክልሉን ምጣኔ ሃብታዊ እድገት 8 በመቶ ለማድረስ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ለዚህም የመንግስትን አገልግሎትን ዲጂታላይዝ ማድረግ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በሙሉ አቅም ወደ ስራ ማስገባት ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ማሳደግ፣ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት እና የስራ ዕድል መፍጠርም በትኩረት የሚሰራባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

በአመርቲ ተስፋዬ

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!