የሀገር ውስጥ ዜና

በጅግጅጋ እና በሚኒያፖሊስ ከተሞች መካከል የእህትማማችነት ትብብር ለማድረግ ከስምምነት ተደረሰ

By Feven Bishaw

August 03, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅግጅጋ እና በአሜሪካዋ ሚኒያፖሊስ ከተማ መካከል የእህትማማችነት ትብብር ለማድረግ ከስምምነት መደረሱ ተገለፀ።

በሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኢብራሂም ኡስማን የተመራው የክልሉ ከፍተኛ ልኡካን ቡድን የሚኒያፖሊስ ማዘጋጃ ቤትን ጎብኝቷል፡፡

ቡድኑ ከከተማው ከንቲባ ጃኮብ ፍሬይ እና የምክር ቤት አባል ከሆኑት ጀማል ኡስማን ጋርም ተወያይቷል፡፡

በውይይቱም በጅግጅጋ እና በሚኒያፖሊስ ከተሞች መካከል የእህትማማችነት ትብብር ለማድረግ ከስምምነት መደረሱን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የፐብሊክ ሰርቪስ ልምድ ልውውጥ ማድረግ የእህትማማች ስምምነቱ አንድ አካል መሆኑም ተገልጿል፡፡ #Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!