Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመሪዎች ደረጃ የተደረጉ ውይይቶች እና ስምምነቶች የሃገርን ዘለቄታዊ ጥቅም ያስጠበቁ መሆናቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሀገር ውጭ በመሪዎች ደረጃ የተደረጉ ውይይቶች እና ስምምነቶች የሃገርን ዘላቂ ጥቅም ያስጠበቁ እንደነበሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው እንዳስታወቁት÷ የሃገራትና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ወደ ሃገር ቤት መጥተው ጉብኝትና የተለያዩ ስምምነቶችን ማከናወናቸው የተሰራው ጠንካራ የገጽታ ግንባታ ተግባር ውጤት ማሳያ ነው፡፡

የሃገራት እና ተቋማት መሪዎች ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ወደ ሃገር ቤት መምጣታቸው በተሰራው የማለዘብና የማስገንዘብ ዲፕሎማሲ ስራ የመጣ ውጤት እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡

የሃገራት እና ተቋማት መሪዎችም የተጀመሩ ሰፊ የልማት እና የትብብር ስራዎችን በአጭር ጊዜ እውን ለማድረግ እና በጋራ የመልማት እቅዶችን ለመተግበር ፍላጎት የታየባቸው መሆኑንም ጠቁመዋል።

ከሃገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በጋራ የመስራቱ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አምባሳደር ምስጋኑ ገልጸዋል።

በፍሬህይወት ሰፊው

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version