አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር በሁለትዮሽ አጀንዳዎች ላይ ተወያዩ።
በውይይታቸውም በየሀገራቱ በሚከናወኑ ኮቪድ19ን የመከላከል መልካም ተሞክሮዎች ላይ መምከራቸውን በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።
ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ እና በሕንድ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ትብብር ያስገኛቸውን ስኬቶች እና ምዕራፎች አጠናክሮ ለማስቀጠል ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ጠቅሰዋል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።