Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደርን ለማሻሻል የሚያግዝ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደርን ለማሻሻል የሚያግዝ ፕሮጀክት ይፋ ተደርጓል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷ ፕሮጀክቱ የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደር ማሻሻያን ተግባራዊ በማድረግ ላይ የሚገኙ ተቋማትን አቅም በመገንባትና ቴክኒካዊ ድጋፍ በመስጠት ጉልህ ሚና ይጫወታል ፡፡

በሚቀጥሉት አራት አመታት ውስጥ ተግባራዊ በሚደረገው ፕሮጀክት የተጠቃሚ ተቋማትን የአመራር አቅም የማጎልበት፣ የተሻሻለ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር አገልግሎትን በታችኛው የመንግስት እርከን የማስፈን ስራ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ÷የበጀት አስተዳደርንና ክትትልን የማሻሻልና የመንግስት ግዢ አገልግሎት ተቋማዊ አቅምን የማሳደግ ተግባር በፕሮጀክቱ ድጋፍ ሰጪ የቴክኒክ ቡድን እንደሚከናወን ተነስቷል፡፡

የቴክኒክ ድጋፉን በቀጣዩ አራት ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል የአውሮፓ ህብረት በአጠቃላይ የ10 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ መመደቡን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version