Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሶማሌ ክልል አልሸባብን ለመደምሰስ በተካሄደው ዘመቻ ለተሳተፉ አካላት እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል አልሸባብ የሽብር ቡድንን ለመደምሰስ በተካሄደው ዘመቻ ለተሳተፉ የክልሉ ፖሊስ አባላትና ለሰራዊቱ ድጋፍ ላደረጉ አካላት እውቅና ተሰጥቷል ፡፡

የእውቅና አሰጣጥ ስነ-ስርዓቱ በአፍዴር ዞን ቆህሌ ወረዳ ዳራዬ ቀበሌ በዛሬው ዕለት ተካሒዷል።

በስነ-ስርዓቱ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮችና ነዋሪዎች መገኘታቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version