Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአዘርባጃን የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሶሻል ኢኖቬሽን ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአዘርባጃን የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሶሻል ኢኖቬሽን ሚኒስትር ኡልቪ ሜዲዬቭ እና ልዑካን ቡድናቸው ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም÷ዘመናዊ እና የተቀላጠፈ አገልግሎት በአንድ ማዕከል መስጠት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም ÷አዲስ አበባ ከተማን የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ምርጥ ተሞክሮ መካፈላቸውን ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስፍረዋል፡፡

በቀጣይ በትብብር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version