ስፓርት

ቢኒያም በላይ እና ዮሴፍ ታረቀኝ የውድድር አመቱ ኮከቦች በመሆን ተመረጡ

By ዮሐንስ ደርበው

July 31, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊሱ ተጫዋች ቢኒያም በላይ የ2015 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች በመሆን ተመረጠ።

‘የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፎትቦለርስ አሶሴሽን’ እንዳስታወቀው ተጫዋቹ፥ በየክለብ አምበሎች በተደረገ ምርጫ ቀዳሚ በመሆን የውድድር አመቱ ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።

ቢኒያም በላይ በዚህ የውድድር አመት ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ሲያነሳ በግሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ይታወሳል።

በተጨማሪም ሜዳ ላይ የሚያሳየው ድንቅ እንቅስቃሴ ለዚህ ሽልማት አሸናፊነት አብቅቶታል።

ከበርካቶች አድናቆት ከዚህ ባለፈም የአዳማ ከተማው ዮሴፍ ታረቀኝ የውድድር አመቱ ኮከብ ወጣት ተጫዋች ሆኖ መመረጡን ‘አሶሴሽኑ’ በላከው መግለጫ አስታውቋል።