Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዶክተር ሊያ የኤካ ኮተቤ የኮሮና ቫይረስ ህክምና ማዕከልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር  ዶክተር ሊያ ታደሰ የኤካ ኮተቤ የኮሮና ቫይረስ ህክምና ማዕከልን ጎበኙ።

የኮሮና ቫይረስ ህመምተኞች ህክምናቸውን በሚከታሉበት በዚህ ማዕከል ባደረጉት ጉብኝት የአገልግሎት አሰጣጡ በእጅጉ መሻሻሉን ማየት እንደቻሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ሙሉ በሙሉ ያገገሙ ህመምተኞችን አግኝተው ያነጋሩ ሲሆን፥ “ባገኙት አገልግሎት ደስተኛ መሆናቸውን መስማቴ አስደሳች ነበር” ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ማዕከሉ ኮቪድ-19 ተገኘባቸው ዜጎች ተለይተው የህክምና አገልግሎት እያገኙበት ይገኛል።

Exit mobile version