Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶርን ዛሬ ከሰዓት በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተቀብለው አነጋግረዋል።

ውይይታችው የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ኢኮኖሚያዊና የንግድ ግንኙነቶችን ለማሳደግ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት ጉዳዮች ላይ ለመተባበር እንዲሁም በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ልማት ጉዳዮች ላይ ለመስራትም መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ከውይይታቸው በኋላም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ አብረው ችግኞችን ተክለዋል።

Exit mobile version