Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሶማሌ ክልል ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ መስጠቱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 11 ቢሊየን 443 ሚሊየን 226 ሺህ ብር ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የሶማሌ ክልል ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ኢብራሂም አሕመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ ፈቃድ የተሰጠባቸው ፕሮጀክቶች 367 ናቸው፡፡

ማዕድን፣ ግብርና፣ እንስሳት ሃብት፣ ኢንዱስትሪ፣ ኮንስትራክሽን፣ ሆቴል፣ ቤት ልማት፣ ንግድ እና አገልግሎት ፈቃድ የተሰጠባቸው ዘርፎች መሆናቸው ተገልጿል።

ፕሮጀክቶቹ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገቡም÷ 12 ሺህ 243 የሥራ ዕድ እንደሚፈጥሩ ይጠበቃ ነው የተባለው፡፡

የኢንቨስትመንት ፍሰቱን በይበልጥ ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑንም ነው አቶ ኢብራሂም የተናገሩት፡፡

የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች በልማት ሥራዎች በንቃት እንዲሳተፉ ቢሮው በትኩረት እየሠራ ስለመሆኑም አመላክተዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶችን ለማነቃቃት በጅግጅጋ ከተማ በ11 ሔክታር ላይ የኢንዱስትሪ መንደር መዘጋጀቱንም ገልጸዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version