ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲን የ12ኛ ክፍል ፈተና ቅድመ ዝግጅት ጎበኙ

By Meseret Awoke

July 25, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የቅድመ ዝግጅትና የተማሪዎች አቀባበል ሁኔታን ተመልክተዋል።

ሚኒስትሩ ከሶማሌ ብሔራዊ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ነው ፈተናውን ቅድመ ዝግጅት የተመለከቱት፡፡

ብርሃኑ (ፕ/ር) በጉብኝታቸው ፥ የዩኒቨርሲቲውን አመራሮችና ተፈታኝ ተማሪዎችን ስለቅድመ ዝግጅቱ ያነጋገሩ ሲሆን ፥ ተፈታኝ ተማሪዎቹም ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ አበረታተዋል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!