የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአምስት ሀገራት መሪዎች ስብሰባ ላይ ተሳተፉ

By Feven Bishaw

July 24, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 17 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ከሰዓት በኋላ የአምስት ሀገራት መሪዎች ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል።

በስብሰባው ኢትዮጵያን ጨምሮ የጣሊያን፣ የጅቡቲ፣ የሶማሊያ እና የኬንያ የመሪዎች መገኘታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ስብሰባው በሀገራቱ መካከል የተቀናጀ ትብብር እንዲኖር የጋራ በሆኑ ጉዳዮች እና ፍላጎቶች ላይ ለመምከር የተዘጋጀ ነው ተብሏል።