Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአፋር ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው፡፡

ለሶስት ቀናት በሚካሄደው ጉባዔ የ2016 በጀት ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም የተለያዩ ተቋማትን አፈፃፀም ሪፖርት እንደሚመለከት ተጠቁሟል፡፡

አሁን ላይም የክልሉ የ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡

Exit mobile version