ስፓርት

በለንደን ዳይመንድ ሊጉ ጉዳፍ ፀጋየ  አሸነፈች

By Mikias Ayele

July 23, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በለንደን ዳይምንድ ሊጉ የ5 ሺህ ሜትር ወድድር  አትሌት ጉዳፍ ፀጋየ ድል ቀንቷታል፡፡

ጉዳፍ  ርቀቱን ለመጨረስ 14 ደቂቃ ከ12 ሴኮንድ የፈጀባት ሲሆን ተቀናቃኞቿን ሲፈን ሀሰን እና ብያትሪስ ቺቤትን በመቅድም ነው የ5 ሺህ ሜትር እርቀቱን በበላይነት ያጠናቀቀችው፡፡

በርቀቱ ኬንያዊቷ ብያትሪስ ቺቤት 2ተኛ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ  እና ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው አትሌት ሲፈን ሀሰን 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡

የኦሪገኑን ድርብ ድል በቡዳፔስት ለመድገም እየተዘጋጀች  የምትገኘው ጉዳፍ ፀጋየ የዛሬው ድሏ በአለም ሻሚዮናው ተጠባቂ አትሌት እንድትሆን አስችሏታል፡፡