የሀገር ውስጥ ዜና

የሚያጠቡ ተፈታኞች ሞግዚት ይዘው እንዲገቡ ተፈቀደ

By ዮሐንስ ደርበው

July 23, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ የሚያጠቡ ተፈታኞች አንድ ሴት ሞግዚት ይዘው እንዲገቡ መፈቀዱን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

መውለጃ ወራቸው የደረሰ ነፍሰ ጡር እና ጡት የሚያጠቡ ተፈታኞች በሚቀጥለው ዓመት ተዘጋጅተው እንደ መደበኛ ተፈታኝ ቢፈተኑ እንደሚመከር አገልግሎቱ አስገንዝቧል፡፡

ይሁን እንጅ ለመፈተን የወሰኑ ከሆነ÷ ጡት የሚያጠቡት ተፈታኞች አንድ ሴት ሞግዚት ይዘው በመግባት እንዲፈተኑ ተገቢው ድጋፍ  ይደረግላቸዋል መባሉን የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

የተፈታኞች መብትና ግዴታ እንዲሁም የተከለከሉ ነገሮች በተመለከተም÷ በተፈታኟና በሞግዚቷ ላይ ተግባራዊ እንደሚደረጉ ነው አገልግሎቱ ያሳሰበው፡፡