የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው

By Feven Bishaw

July 21, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ የፋይናንስ ጉዳዮች፤ የኢኮኖሚ ዕቅድና ውህደት ላይ ያተኮረው የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

 

6ኛው የፋይናንስ ጉዳዮች፣ የኢኮኖሚ ዕቅድና ውህደት ላይ ያተኮረው የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ጉባኤ በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

 

በጉባኤው የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ጥሩማር አባተ በሚኒስትሮች ደረጃ በሚደረገዉ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡