Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በዓለም የውሀ ስፖርቶች ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሽኝት ተደረገለት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ20ኛው የዓለም ውሀ ስፖርቶች ሻምፒዮና ላይ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት ዛሬ ሽኝት ተደረገለት።

በጃፓን ፎካካ በሚካሄደው ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በአንድ ወንድና ሴት አትሌቶች በ50 ሜትር ነፃ ቀዘፋ እና ቢራቢሮ ትካፈላለች።

የዓለም ውሃ ሻምፒዮና ተወዳዳሪዎች ከሁሉም ክልሎች የመጡ እና የማጣሪያ ውድድር በፌዴሬሽኑ አማካኝነት አድርገው የተሻለ ሰዓት ያስመዘገቡት ናቸው ተብሏል።

ውድድሩ ከሃምሌ 14 እስከ 21 የሚካሄድ ሲሆን÷ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ማታ ወደ ጃፓን ጉዞውን ያደርጋል፡፡

በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ ጨምሮ ከ195 ሀገራት የተወጣጡ 2 ሺህ 392 አትሌቶች ተካፋይ ይሆናሉ ተብሏል።

የጃፓን ፎካካ ከተማ ከእዚህ ቀደም ከ22 አመት በፊት ተመሳሳይ ውድድር አስተናግዳለች፡፡

በወርቅነህ ጋሻሁን

Exit mobile version