አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 26 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ1 ሺህ 758 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 5 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው ውስጥ አራቱ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ፥ አንደኛው ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ የስዊድን ዜጋ ነው ተብሏል።
ከእነዚህ መካከል አንደኛው የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ የሆነ የ17 አመት ታዳጊ ሲሆን፥ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንከኪ የነበረው ነው።
ሶስቱ ኢትዮጵያውያን የ20፣ 23 እና 24 አመት ወጣት ሲሆኑ ከፑንትላንድ የተመለሱና በጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ናቸው።
ስዊድናዊው ዜጋ የ19 አመት ወጣት ሲሆን፥ ከስዊድን የተመለሰና በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኝ መሆኑ ተገልጿል።
አሁን ላይ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 140 የደረሰ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ 60ዎቹ በለይቶ ህክምና ውስጥ የሚገኙ ናቸው።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision