አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት አመቱ 203 አገልግሎቶችን በማቅረብ 75 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የኢትዮ ቴሌኮም የ2015 በጀት አመት የስራ አፈፃፀምን በሚመለከት ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
በማብራሪያቸውም በበጀት አመቱ በተሰራ ስራ የሞባይል ኔትዎርክ እና የብሮድባንድ ኔትዎርክ ሽፋንን ማሳደግ ተችሏል ብለዋል፡፡
ተቋማቸው በበጀት አመቱ ከሚሰጣቸው 203 ምርት እና አገልግሎቶች 75 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቀዋል።
አፈጻጸሙ ከእቅድ በላይ መሆኑን ጠቅሰው÷በበጀት አመቱ የውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች የተገኘው ገቢ 164 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በበጀት አመቱ 264 ከተሞች የሞባይል የ4ጂ አገልግሎት ማግኘት መቻላቸው ጠቁመዋል፡፡
በፍቅርተ ከበደ