የሀገር ውስጥ ዜና

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ተካሄደ

By Amare Asrat

July 15, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር የምርጫ ዘመን 3ኛ የስራ አመት 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ተካሂዷል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንታዬ ከበደ እንዳሉት፥ በጉባኤው የዞን አስተዳደሮች ሹመት ተሰጥቷል።

ባለፈው የበጀት አመት ክልሉ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱንም ጠቅሰዋል፡፡

የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ሰፊ ስራ መሰራቱንም ነው ለአብነት ያነሱት፡፡

ክልሉ በሶስት አመታት ውስጥ የተገበራቸውን ውጤታማ ስራዎች በተያዘው የበጀት አመትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

መቅደስ አስፋውና ደብሪቱ በዛብህ