አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጀርመን የ25 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ።
የድጋፍ ስምምነቱ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በጀርመን ልማት ባንክ የአፍሪካ ህብረት እና የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ክርስቶፍ ቲስኬንስ ተፈራርመውታል።
ድጋፉ በገጠራማው የሀገሪቱ ክፍል ያለውን የግብርና ሰንሰለት ለማጠናከር የሚተገበረውን ፕሮጀክት ለማሻሻል የሚያግዝ ነው ተብሏል።
ይህም በምስራቅ ጎጃም እና አርሲ ዞኖች የሚተገበር መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
የዚህ ፕሮጀክት ዋና አላማ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ እና ዘላቂነት ያለው ሥነ ምህዳር ለመተግበር፥ የግብርና ምርታማነትን መጨመር እና ከፍተኛ የዝናብ መጠን በሚያገኙ አካባቢዎች የገበያ ተደራሽነትን ማስፋት መሆኑ ተጠቅሷል።