ቢዝነስ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ 107 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

By Shambel Mihret

July 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ በበጀት አመቱ 107 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ።

ገቢው በገቢዎች ቢሮ፣ በማዕከል ተቋማት እና በክፍለ ከተሞች የተሰበሰበ መሆኑን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ አደም ኑሪ ተናግረዋል።

ገቢው ከአምናው የበጀት አመት ጋር ሲነፃፀር የ38 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለውም ተገልጿል፡፡

ቢሮው የ2015 በጀት አመት የገቢ እቅድ ማጠቃለያ እና የ2016 በጀት አመት የግብር ማሳወቂያ ንቅናቄ መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ ግብር ፍትሃዊነትን ማስፈኛ ዋነኛ መንገድ ነው ብለዋል፡፡

የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የገቢ ሰራተኞችና ግብር በታማኝነት ለከፈሉ ነጋዴዎችም እውቅና ተሰጥቷል።

በ2016 በጀት አመትም 140 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱም ተጠቅሷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ከንቲባ  አዳነች አቤቤን ጨምሮ የመከላከያ ሚኒስትሩ አብርሀም በላይ (ዶ/ር) እና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል፡፡

በሲሳይ ዱላ እና ፍቅርተ ከበደ