የሀገር ውስጥ ዜና

በሕገ ወጥ መንገድ ሲጋራ ሲያዘዋውሩ የነበሩ 3 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

By ዮሐንስ ደርበው

July 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ3 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያለው ሲጋራ በሕገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሦስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው፡፡

ሲጋራው በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ሲል በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጎሮጉቱ ወረዳ ከሌሊቱ 6፡00 አካባቢ በፀጥታ ኃይል መያዙ ተገልጿል፡፡

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ዲቪዥን ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ቶሎሳ ጎሹ እንደገለጹት÷ የተያዘው 200 ካርቶን ሲጋራ ወደ ድሬዳዋ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ገቢ ተደርጓል፡፡

በተሾመ ኃይሉ