Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በ24 ሰዓታት ውስጥ ለ2 ሺህ 16 ሰዎች የምርመራ ቢደረግም የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ሰው የለም

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባላፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለ2 ሺህ 16 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ ቢደረግም የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት አንድም ሰው አለመኖሩን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት በትናንትናው እለት ሶስት ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ይህንንም ተከትሎ በሀገሪቱ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 69 ደርሷል።

በኢትዮጵያ እስካሁን ለ19 ሺህ 857 ሰዎች የኮቪድ-19 ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 133 ናቸው።

 

Exit mobile version