የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደስታ ሌዳሞ የክልሉን የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አስጀመሩ

By Amare Asrat

July 08, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የክልሉን የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አስጀመሩ።

 

“በጎ ፈቃደኝነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሀሳብ የሲዳማ ክልል የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በይርጋዓለም ከተማ እየተካሄደ ነው።

 

በሲዳማ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አዘጋጅነት የክረምት ወራት ወጣቶች የበጎ ፍቃድ መርሐ ግብር ማስጀመሪያ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የሲዳማ ብሄራዊ ክልል ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደን ጨምሮ የክልሉ የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸው የክለሉ መስተዳድር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

 

በመርሐ-ግብሩ ከ612 ሺህ በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።