Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባህርዳር ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና የመጨረሻ ጨዋታቸውን በድል አጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል።

 

ቀደም ብሎ ከወላይታ ዲቻ ጋር የተጫወቱት የጣና ሞገዶቹ ባህር ዳር ከተማ በአደም አባስ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡

 

ውጤቱን ተከትሎም ባህርዳር ከተማ ነጥቡን 60 በማድረስ በሊጉ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል፡፡

 

ወላይታ ዲቻ በአንፃሩ ላለመውረድ ከፍተኛ ትግል ሲያደርግ ቆይቶ በ37 ነጥብ 12ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል፡፡

 

አመሻሽ ላይ ከኢትዮጵያ መድን የተጫወቱት ሀዲያ ሆሳዕናዎች በሰመረ ሀፍታይ እና ተመስገን ብርሃኑ ጎሎች 2 ለ 0 አሸንፈዋል።

 

ውጤቱን ተከትሎም ሀዲያ ሆሳዕና በ43 ነጥብ 6ኛ ደረጃን እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን በ49 ነጥብ 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

 

Exit mobile version