አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ትራንሽን ማኑፋክቸሪንግ (ቴክኖ ሞባይል) የካሞን 20 ሲሪየስ ሞዴል ስልክን በኢትዮጵያ አስተዋወቀ ።
ኩባንያው በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቀው ካሞን 20 ሲሪየስ ሞዴል ስልክ ዘመናዊና የዓለም የሞባይል ቴክኖሎጂ ዕድገትን የሚያሳይ ነው ተብሏል።
ስልኩ በ108 ሜጋ ፒክስል ካሜራ ፎቶ እና ቪዲዮ በጥራት ማንሳት የሚያስችል የኤስ.ኤል,አር ሲስተም የሚታገዝ ባለ ሁለት ሌንስ ካሜራ እንዲሁም በምሽት ጥራት ያለው 50 ሜጋ ፒክስል ምስል ማንሳት ያሚያስችል አር ጂ ቢ ደብሊው ሴንሰር የተገጠመለት መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም 45ዋት በፍጥነት ቻርጅ የማድረግ አቅም ያለው ባለ 5 ሺህ አምፒር ባትሪ የያዘ መሆኑም ነው የተነገረው።
ትራንሽን ማኑፋክቸሪንግ የተለያዩ ስልኮችን ሀገር ውስጥ በመገጣጠም ለሀገር ውስጥ እና ለውጪ ገበያ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል።
አዲስ ያስተዋወቀው ስልክም ቴክኖ ሞባይል ዓለም አቀፍ ሽልማት ያገኘበትን ብሎም ጊዜው የደረሰበትን የስልክ ቴክኖሎጂ እንደያዘ በማስተዋወቂያ ፕሮግራሙ ላይ ተጠቅሷል።
በማህሌት ተክለብርሐን