የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ፖላንድ የታክስ ትብብር ሰምምነት ተፈራረሙ

By Mikias Ayele

July 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ፖላንድ የታክስ ትብብርን ማጠናከር የየሚያስችል ምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረት የሑለቱ ሀገራት የታክስ ትብብር ፕሮግራሙ ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት ተግበራዊ እንደሚደረግ ነው የተገለፀው፡፡

ስምምነቱ በተለይም የገንዘብ ሚኒስቴር እና ገቢዎች ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች በተለያዩ የታክስ አይነቶች ስልጠኛዎችን መስጠት እንዲችሉ፣የበየነ መረብ ውይይት እና ጥናቶችን እንዲያደርጉ የሚስችል ነው ተብሏል፡፡

ስምምነቱ በገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እና በኢትዮጵያ የፖላንድ አምባሳድር ፕሪዚሚሰሎው ቦባክ መካከል መፈረሙን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡