ስፓርት

የፊታችን ሐምሌ 8 ቀን የኢትዮጵያ የፕሪሚየር ሊግ ተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ይከፈታል

By ዮሐንስ ደርበው

July 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፊታችን ሐምሌ 8 ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ወንዶች እና ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ተጫዋቾች የዝውውር መስኮት እንደሚከፈት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡

የዝውውር መስኮቱ ከሐምሌ 8 ቀን እስከ መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡

የተጫዋቾች ዝውውር ሕጋዊነት የሚፀድቀውም÷ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ጽሕፈት ቤት ተገኝቶ በመፈራረም ብቻ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በክልል እግር ኳስ ፌደሬሽኖች እና በሌላ አካል በኩል የሚደረግ ስምምነት ተቀባይነት የለውም መባሉን   የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡