Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ እንዲሳካ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጥናት የተደገፈ የምርታማነት ማሻሻያ ሥራዎችን በማከናወን የ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ እንዲሳካ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና በተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ጉባዔ፤ በኢትዮጵያ “ሁሉን አቀፍ የምርታማነት አቅም ማሳደጊያ ፕሮግራም” ጥናት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጎበታል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) ÷ የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ጉባዔ ላለፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ምርትና ምርታማነት ያሉበትን ክፍተቶች መለየት የሚያስችል ጥናት አድርጓል ብለዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል በበኩላቸው ÷በማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ጉባዔ የአፍሪካ ዳይሬክተር ፓውል አኪዩሚ÷ በየትኛውም አገር የኢኮኖሚ ክፍተቶችና ተግዳሮቶች የሚያጋጥሙ መሆኑን ጠቅሰው በኢትዮጵያም ተመሳሳይ ችግሮች ስለመኖራቸው ማንሳታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version