አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ልዑክ ካናዳ ቶሮንቶ ከተማ ገብቷል።
ልዑኩ ካናዳ የገባው በቶሮንቶ ለሚካሄደው 25ኛው አለም ዓቀፍ የሀረሪ የባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል ለመሳተፍ ነው።
የልኡካን ቡድኑ ካናዳ ቶሮንቶ ሲደርስም በሀረሪ ኮሙዩኒቲ አባላት አቀባበል ተደርጎለታል።
25ኛውን አለም ዓቀፍ የሀረሪ የባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል በተለያዩ መርሃግብሮች እንደሚከበር ለማወቅ ተችላል።
ልዑኩ ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ፣ የክልሉ ምክር ቤት ም/አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ግንባታ ማእከል ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ካሊድ አልዋን እንደሚገኙበት ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።