የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያንና የጅቡቲን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የባቡር ጉዞ እየተደረገ ነው

By Amele Demsew

July 02, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያንና የጅቡቲን ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክራል የተባለለት ጉዞ ከጅቡቲ ኢትዮጵያ በባቡር እየተደረገ ነው፡፡

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) እና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባዘጋጀው ጉዞ 100 የሚሆኑ የጅቡቲ ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ።

የጉዞውን አላማ በማስመልከት የመክፈቻ ንግግር ያረጉት በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ጉዞው በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት ብለዋል።

ታሪካዊውን የሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት በባህል፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚ ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም ነው የተናገሩት፡፡

የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ከሌሎች አባል ሃገራት በተለየ መልካም ግንኙነት ያላቸውን ሁለቱን ሃገራት በመሰል ተግባራት ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ ታምራት