ዓለምአቀፋዊ ዜና

በኬንያ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ49 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Melaku Gedif

July 01, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ ምዕራባዊ ግዛት በፍጥነት መንገድ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ከ49 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው ኮንቴነር የጫነ ተሳቢ መኪና ከአሽከርካሪው ቁጥጥር ውጪ በመሆኑ እንደተከሰተ የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በአደጋው ለህልፈት ከተዳረጉት በተጨማሪ 30 በላይ ዜጎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡

ጉዳት የደረሳባቸው ሰዎች አቅራቢያ በሚገኝ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡