የሀገር ውስጥ ዜና

የተመድ የስነ-ሕዝብ ፈንድ ከኢትዮጵያ  ጋር ያለው ትብብር እንደሚያጠናክር ገለጸ

By Shambel Mihret

June 29, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)  አዲስ ከተሾሙት የተባባሩት መንግስታት ደርጅት የስነ-ሕዝብ ፈንድ የኢትዮጵያ ተወካይ ኮፊ ኩዋሜ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)÷ተወካዩ በቆይታቸው በስነ-ሕዝብ ዘንድ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለማጠናከር ትብብራቸውን እንደሚያጎለብቱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

መንግስት የስነ-ሕዝብን ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ጠቅሰው÷በሀገሪቱ የልማት እቅዶች ውስጥ በማካተት እተገበረ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ኮፊ ኩዋሜ በበኩላቸው ÷ የተባበሩት መንግስታት የስነ-ሕዝብ ፈንድ ከኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ ጋር በስነ-ሕዝብ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰራቸውን የትብብር ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ቆይታቸው የሕዝብን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ የትብብርና የልማት አጋርነት ተግባራትን ለማጎልበት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡