የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከፍተኛ የጸጥታ አመራሮች እየተወያዩ ነው

By Shambel Mihret

June 29, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከፍተኛ የጸጥታ አካላት የቀጣናውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል በቻግኒ ከተማ እየመከሩ ነው።

የከፍተኛ አመራሮች የጋራ ምክክር መድረክ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ያለውን ሰላም እና አብሮነት ለማስቀጠል ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የሕዝቦችን የጋራ የልማትና የሰላም ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ የጸጥታ አካላት እስከ ወረዳ ያለውን አሁናዊ የሰላምና ጸጥታ ጉዳይ በመፈተሽ የጋራ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ደሳለኝ ጣሰው፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደጀኔ ልመንህ  እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቢዮት አልቦሮ ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም የመተከል ዞንና አዋሳኝ ወረዳዎች፣ የምዕራብ ጎጃም፣ ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎደንደርና አዊ ዞን አስተዳዳሪዎች የጸጥታ አካላት እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች መሳተፋቸውን የመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡