Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የስልጤ ባሕላዊ ምግብ “አተካኖ” በአፍሪካ ድንቃድንቅ ተመዘገበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከስልጤ ባሕላዊና የክብር ምግቦች መካከል አንዱ የሆነው “አተካኖ” በአፍሪካ ድንቃድንቅ ተመዘገበ።

በአፍሪካ ድንቃድንቅ የተመዘገበው “አተካኖ” ከ8 ሜትር በላይ ርዝመት እና 10 ሴንቲሜትር ጥልቀት እንዳለው ተገልጿል፡፡

ይህ ባህላዊ ምግብ በርዝመቱ እና በልዩ ጣዕሙ በአፍሪካ ድንቃድንቅ አንደኛ ሆኖ ስለመመዝገቡ የአፍሪካ ድንቃድንቅ ዋና ዳይሬክተር አሸናፊ ዓለም አረጋግጠዋል፡፡

ለዚህም ዳይሬክተሩ የባለቤትነትና የእውቅና የምስክር ወረቀት ለስልጤ ዞን አስተዳደር አስረክበዋል።

“አተካኖ” በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ምግብ ቤቶች የምግብ ዝርዝር ውስጥ እንዲካተት መትጋት እንደሚገባም መክረዋል፡፡

የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዓሊ ከድር በበኩላቸው÷ ባሕላዊና የክብር ምግብ የሆነው “አተካኖ” ከቀደምት የስልጤ አያቶች ከትውልድ ትውልድ ስለመሸጋገሩ ገልጸዋል፡፡

በአፍሪካ ድንቃድንቅ ውስጥ መካተቱና ለዚህም እውቅና ማግኘቱ የብሔረሰቡን ባሕላዊ ምግብ ይበልጥ የማስተዋወቅ ዕድል ይፈጥራል ማለታቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ምግቡ ከማሕበረሰቡ ውጪ በሌሎችም እንዲታወቅ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version