Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሲዳማ ክልል መስተዳድር ም/ቤት የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገመ ነው፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተደድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ÷የዓመቱን ሥራ በጊዜ ገምግሞ በማጠቃለል በፍጥነት የ2016 በጀት ዓመት ሥራ ለመጀመር ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

ምክር ቤቱ የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት ከየቢሮ ተዘጋጅቶ የቀረበውን ጥራት እና ወቅታዊ የሕዝብ ጥያቄዎችን የሚመልስ መሆኑ እንደሚያረጋጥ ተጠቁሟል፡፡

በቀጣይም ወደ ተግባር እዲሸጋገር በመስተዳድር ምክር ቤት ደረጃ ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የርዕሰ መስተዳድሩ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

 

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version