አዲስ አበባ፣ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በካናዳ የተከሰተው ሰደድ እሳት እስካሁን 7 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር በላይ ደን ማቃጠሉ ተሰምቷል፡፡
ይህም ክስተቱን እስከ አሁን ታይቶ የማይታወቅ የሰደድ እሳት አደጋ አድርጎታል ነው የተባለው፡፡
ሀገሪቱ ለሰደድ እሳት አደጋ ቅድመ ዝግጅት እና ጥንቃቄ ብታደርግም÷ቃጠሎው ከተጠበቀው በላይ ተባብሶ መቀጠሉን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
በዶኒ ክሪክ ውስጥ በተቃጠለ ትልቅ ጫካ ውስጥ ጠፍቶ የነበረው የሰደድ እሳት እንደገና መቀስቀሱም ተነግሯል።
አሁን ላይ በአካባቢው የተቃጠለው የደን ሥፍራ ከ550 ሺህ ሄክታር በላይ ሲሆን÷ በፈረንጆቹ 2017 ከተከሰተው ተመሳሳይ የደን ቃጠሎ ጋር ሲነፃፀር በእጅጉ እንደሚበልጥ ተመላክታል፡፡