Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኮንትሮባንድ የገቡ የተለያዩ ሞባይል ስልኮች እና የብር ጌጣጌጦች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮንትሮባንድ የገቡ የተለያዩ ሞባይል ስልኮች እና የብር ጌጣጌጦች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አዲስ አበባ የገበያ ማዕከል አካባቢ ነው ከሕብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ  የተያዙት፡፡

በዚህም ምንም ዓይነት ቀረጥ ሳይከፈልባቸው በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡና በስድስት ካርቶን የታሸጉ የተለያዩ ጌጣጌጦችና ብዛታቸው 970 የሚሆኑ የሞባይል ስልኮች መያዛቸው ተገልጿል፡፡

ፖሊስ በዚህ ድርጊት ተሳታፊ የሆነ ተጠርጣሪንም ከእነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ  እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡

Exit mobile version