የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው

By Amele Demsew

June 23, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሁለተኛው ምዕራፍ የመጀመሪያ ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ጎሃ ቀበሌ እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)፣ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢያሱ ኤልያስ (ፕ/ር) እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ኃይለማርያም ከፍያለው (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች ተገኝተዋል።

በአማራ ክልል በሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ የመጀመሪያው ዓመት 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ግብ ተይዞ ወደ ሥራ መገባቱ ተገልጿል።

በክልሉ ለደን እና ለምግብነት የሚያገለግሉ የፍራፍሬና ሌሎች ችግኞች ላይ ትኩረት ተደርጎ የሚካሄደው የችግኝ ተከላ ከ201 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት እንደሚሸፈን መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በክልሉ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በተሰራው ተከታታይ ሥራ የደን ሽፋኑ 16 በመቶ ደርሷል ተብሏል፡፡

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!