ቢዝነስ

አማራ ባንክ ካፒታሉን 6 ቢሊየን ብር ማድረሱን አስታወቀ

By Meseret Awoke

June 22, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አማራ ባንክ የተከፈለ ካፒታሉን 6 ቢሊየን ብር ማድረሱን አስታውቋል፡፡

ባንኩ አንደኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ይገኛል፡፡

በመርኃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሔኖክ ከበደ ፥ ባንኩ 28 ቢሊየን ብር ንብረት ማፍራቱን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በአሁኑ ሰአት 19 ቢሊየን ብር ተቀማጭ እንዳለውና 15 ቢሊየን ብር ደግሞ ለደንበኞቹ ብድር መስጠቱንም ነው ዋና ስራ አስፈፃሚው የገለፁት።

በአሁኑ ወቅት ባንኩ የተከፈለ ካፒታሉ ስድስት ቢሊየን ያደረሰ ሲሆን ፥ በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ 260 ቅርንጫፎቹ 1 ሚሊየን ደንበኞች እንዳሉትም ተጠቁሟል፡፡

ባንኩ ከመደበኛ የባንክ አገልግሎት በተጨማሪ በውስጥ አቅም የበለፀገ ዘመናዊ የሞባይል ባንክ አገልግሎት፣ የኤ ቲ ኤም፣ የፖስ እንዲሁም ራሱን ችሎ የተቋቋመ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለተጠቃሚው ህብረተሰብ እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

በፍቅርተ ከበደ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!