አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በላቦራቶሪ የተፈበረከ ሥጋ ለገበያ እንዲቀርብ ፈቅጃለሁ ብላለች፡፡
ይህን ተከትሎም አሜሪካ ከሲንጋፖር ቀጥላ በዓለም ላይ በላቦራቶሪ የሚፈበረክ ሥጋ ሽያጭ ላይ እንዲውል የፈቀደች ሀገር ሆናለች።
ደቡብ አፍሪካ በዚሁ መንገድ ሥጋ ማምረት መጀመሯን አምና ይፋ ብታደርግም እስካሁን ለገበያ እንዳላቀረበች ተገልጿል።
በዚህ ሂደት ከከብት ለምሳሌ ከላም ትከሻ አካባቢ ከቃሪያ ፍሬ ያልበለጠ ሥጋ ቅንጣቢ ተወስዶ በላቦራቶሪ ውስጥ እንዲፋፋ እና እንዲጎለምስ ከተደረገ በኋላ ብዙ ኪሎ ሥጋ ሆኖ ይመረታል፡፡
ከትከሻዋ አካባቢ ቅንጣቢው ሴል የተወሰደባት ላም የሚገጥማት እንከን ሳይኖርና በህይወት እያለች ተጨማሪ ሥጋ እንዲመረት ምክንያት ሆነች እንደማለት ነው፡፡
በዚህ ሳይንሳዊ ዘዴ የሚመረት ሥጋ ለምግብነት እንዲውል ወደ ገበያ የመውጣቱ ጉዳይ አከራካሪነቱ እንደቀጠለ መሆኑን አልጄዚራና ዘ-ኦብዘርቨር ዘግበዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!